የፋይናንስ አካታችነት እንዲሻሻል የባንክ መደበኛ አገልግሎቶች በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ቢታገዙ ይበጃል 

የባንኮች ቁጥር መጨመር ውድድርን እንደሚፈጥር ይታመናል። ይህ ውድድር ደግሞ የፋይናንስ አገልግሎቶች ተደራሽነት ያሰፋል ፣ የወለድ ህዳግ (በብድር እና ቁጠባ መካከል ያለው የወለድ ምጣኔ ልዩነት) እንዲጠብ ያደርጋል፣ የደንበኞች ግልጋሎትን ያሻሽላል እንዲሁም አዳዲስ የአሰራር ፈጠራዎችን ያበረታታል።

ነገር ግን እነዚህ ውድድር ያመጣቸዋል ተብለው የሚታሰቡ ትሩፋቶች በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ አወቃቀር ምክንያት እውን ያለመሆን እድላቸው በግልጽ ይታያል።