ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በድሬዳዋ

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ቅድሚያ ከሰጣቸው አጀንዳዎች አንዱ የሃገሪቱን ዲጂታል ኢኮኖሚ አቅም ማሳደግ ነው። ሃገሪቱ ቀስ በቀስም ቢሆን ዲጂታላይዜሽን የኢኮኖሚ እድገትን በማሳለጥ ረገድ የሚኖረውን ጉልህ አስተዋጽኦ የተረዳች ይመስላል። መንግስትም የዲጂታላይዜሽን ትልሞችን ተግባራዊ ለማድረግ በ2012 ዓ.ም ‘ዲጂታል ኢትዮጲያ 2025’ በሚል የሰየመውን ፍኖተ-ካርታ ይፋ በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል። አስተዳደሩ እንደ መሪ ስትራቴጂክ እቅድ የነደፈው ይህ ፍኖተ […]

የፋይናንስ አካታችነት እንዲሻሻል የባንክ መደበኛ አገልግሎቶች በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ቢታገዙ ይበጃል 

የባንኮች ቁጥር መጨመር ውድድርን እንደሚፈጥር ይታመናል። ይህ ውድድር ደግሞ የፋይናንስ አገልግሎቶች ተደራሽነት ያሰፋል ፣ የወለድ ህዳግ (በብድር እና ቁጠባ መካከል ያለው የወለድ ምጣኔ ልዩነት) እንዲጠብ ያደርጋል፣ የደንበኞች ግልጋሎትን ያሻሽላል እንዲሁም አዳዲስ የአሰራር ፈጠራዎችን ያበረታታል።

ነገር ግን እነዚህ ውድድር ያመጣቸዋል ተብለው የሚታሰቡ ትሩፋቶች በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ አወቃቀር ምክንያት እውን ያለመሆን እድላቸው በግልጽ ይታያል።